የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግና የመረጃን ከጊዜ ጋር ማዘመንን በማሰብ በPHEM-DHIS2 ላይ በሶስት ዙሮች ከዞን ወረዳ እና ከጤና ፋስልቲዎችን አካቶ ይሰጥ የነበረው ስልጠና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የስልጠናው ተሳታፊዎች በማጠቃለያ በነበረው መድረክ ላይ ገልፀዋል፡፡ በተያያዘ ዜናም ተሳታፊዎቹ መረጃዎችን ሳይቆራረጡና ሳይንጠባጠኑ በጊዜ ለውሳነ ለመጠቀም እጅጉን ልረዳ የሚችል የዲጂታል መረጃ መሰቢሰቢያ መሆኑን ገልጸው በተገቢው ስራ ላይ ለማዋልም በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡